LibreOffice 24.8 እርዳታ
እርስዎ በ ሰነዱ ውስጥ መቃኘት እና በ ፊደል ገበታ መምረጥ ይችላሉ
የ አይጥ መጠቆሚያውን ለማንቀሳቀስ: ይጫኑ ቁልፍ ወይንም የ ተጣመረ ቁልፍ በሚቀጥለው ሰንጠረዥ ውስጥ
በሚንቀሳቀስ መጠቆሚያ ውስጥ ባህሪዎችን ለ መምረጥ: በ ተጨማሪ ተጭነው ይያዙ የ Shift ቁልፍ እርስዎ መጠቆሚያውን በሚያንቀሳቅሱ ጊዜ
| ቁልፍ | ተግባር | + | 
|---|---|---|
| የ ቀኝ: የ ግራ ቀስት ቁልፎች | መጠቆሚያውን አንድ ባህሪ ወደ ግራ ወይንም ወደ ቀኝ ማንቀሳቀሻ | መጠቆሚያውን አንድ ቃል ወደ ግራ ወይንም ወደ ቀኝ ማንቀሳቀሻ | 
| ወደ ላይ: ወደ ታች የ ቀስት ቁልፎች | መጠቆሚያውን አንድ መስመር ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች ማንቀሳቀሻ | () የ አሁኑን አንቀጽ ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች ማንቀሳቀሻ | 
| ቤት | መጠቆሚያውን ወደ አሁኑ መስመር መጀመሪያ ማንቀሳቀሻ | መጠቆሚያውን ወደ አሁኑ ሰነድ መጀመሪያ ማንቀሳቀሻ | 
| ቤት በ ሰንጠረዥ ውስጥ | መጠቆሚያውን ወደ አሁኑ ይዞታዎች በ አሁኑ ክፍል መጀመሪያ ማንቀሳቀሻ | መጠቆሚያውን ወደ ይዞታው መጀመሪያ ያንቀሳቅሰዋል ወደ አሁኑ ክፍል: በድጋሚ ይጫኑ መጠቆሚያውን ለማንቀሳቀስ ወደ መጀመሪያው ክፍል በ ሰንጠረዡ ውስጥ: በድጋሚ ይጫኑ መጠቆሚያውን ለማንቀሳቀስ ወደ ሰነዱ መጀመሪያ | 
| መጨረሻ | መጠቆሚያውን ወደ አሁኑ መስመር መጨረሻ ማንቀሳቀሻ | መጠቆሚያውን ወደ አሁኑ ሰነድ መጨረሻ ማንቀሳቀሻ | 
| መጨረሻ በ ሰንጠረዥ ውስጥ | መጠቆሚያውን ወደ አሁኑ ክፍል ይዞታዎች መጨረሻ ማንቀሳቀሻ | መጠቆሚያውን ወደ ይዞታው መጨረሻ ያንቀሳቅሰዋል ወደ አሁኑ ክፍል: በድጋሚ ይጫኑ መጠቆሚያውን ለማንቀሳቀስ ወደ መጨረሻው ክፍል በ ሰንጠረዡ ውስጥ: በድጋሚ ይጫኑ መጠቆሚያውን ለማንቀሳቀስ ወደ ሰነዱ መጨረሻ | 
| ገጽ ወደ ላይ | መሸብለያ አንድ ገጽ ወደ ላይ | መጠቆሚያውን ወደ ራስጌ ማንቀሳቀሻ | 
| ገጽ ወደ ታች | መሸብለያ አንድ ገጽ ወደ ታች | መጠቆሚያውን ወደ ግርጌ ማንቀሳቀሻ |